4 እርሷም ማመዛዘን ለጐደላቸው፣“ማስተዋል የሌላችሁ ሁሉ ወደዚህ ኑ” አለች።
5 “ኑ፤ ምግቤን ተመገቡ፤የጠመቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።
6 የሞኝነት መንገዳችሁን ተዉ፤ በሕይወት ትኖራላችሁ፤በማስተዋልም መንገድ ተመላለሱ።
7 “ፌዘኛን የሚገሥጽ ሁሉ ስድብን በራሱ ላይ ያመጣል፤ክፉውን ሰው የሚዘልፍ ሁሉ ውርደት ያገኘዋል።
8 ፌዘኛን አትዝለፈው፤ ይጠላሃል፤ጠቢብን ገሥጸው፤ ይወድሃል።
9 ጠቢብን አስተምረው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ጻድቁን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀቱን ይጨምራል።
10 “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፤