8 ፌዘኛን አትዝለፈው፤ ይጠላሃል፤ጠቢብን ገሥጸው፤ ይወድሃል።
9 ጠቢብን አስተምረው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ጻድቁን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀቱን ይጨምራል።
10 “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፤
11 ዘመንህ በእኔ ምክንያት ይረዝማልና፤ዕድሜም በሕይወትህ ላይ ይጨመርልሃል።
12 ጠቢብ ብትሆን ጥበበኛነትህ ለራስህ ነው፤ፌዘኛ ብትሆን የምትጐዳው ያው አንተው ነህ።”
13 ጥበብ የለሽ ሴት ለፍላፊ ናት፤እርሷም ስድና ዕውቀት የለሽ ናት።
14 በቤቷ ደጃፍ ላይ ትጐለታለች፤በከተማዪቱ ከፍተኛ ቦታ በመቀመጫ ላይ ትቀመጣለች።