አሞጽ 2:2-8 NASV

2 የቂርዮትን ምሽጎች እንዲበላ፣በሞዓብ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤ሞዓብ በጦርነት ጩኸትና በመለከት ድምፅ መሐል፣በታላቅ ሁካታ ውስጥ ይሞታል።

3 ገዧን እደመስሳለሁ፣አለቆቿንም ሁሉ ከንጉሥዋ ጋር እገድላለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።

4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ይልቁን ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና።

5 የኢየሩሳሌምን ምሽጎች እንዲበላ፣በይሁዳ ላይ እሳት እሰዳለሁ።

6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የእስራኤል ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ጻድቁን ስለ ጥሬ ብር፣ችግረኛውንም ስለ ጥንድ ጫማ ይሸጡታልና።

7 የድኾችን ራስ፣ በምድር ትቢያ ላይይረግጣሉ፤ፍትሕንም ከጭቊኖች ይነጥቃሉ፤አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ይተኛሉ፤እንዲህም እያደረጉ ቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ።

8 በመያዣነት በተወሰደው ልብስ ላይ፣በየመሠዊያው ሥር ይተኛሉ፤በአምላካቸው ቤት፣በመቀጫነት የተወሰደውን የወይን ጠጅ ይጠጣሉ።