ዘካርያስ 9:5-11 NASV

5 አስቀሎና አይታ ትርዳለች፤ጋዛ በሥቃይ ትቃትታለች፤አቃሮናም እንደዚሁ ትሠቃያለች፤ ተስፋዋ ይመነምናልና።ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች።

6 ድብልቅ ሕዝቦች አዛጦንን ይይዛሉ፤የፍልስጥኤማውያንንም ትምክሕት እቈርጣለሁ።

7 ደሙን ከአፋቸው፣የተከለከለውንም ምግብ ከመንጋጋቸው አወጣለሁ።የተረፉት ለአምላካችን ይሆናሉ፤በይሁዳም አለቆች ይሆናሉ፤አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።

8 እኔ ግን ቤቴንከዘራፊ ኀይሎች እጠብቃለሁ፤ጨቋኝ ከእንግዲህ ሕዝቤን አይወርስም፤አሁን ነቅቼ እጠብቃለሁና።

9 አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖወደ አንቺ ይመጣል።

10 ሠረገሎችን ከኤፍሬም፣የጦር ፈረሶችን ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ፤የጦርነቱም ቀስት ይሰበራል፤ሰላምን ለአሕዛብ ያውጃል፤ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፣ከወንዙም እስከ ምድር ዳር ድረስ ይዘረጋል።

11 ለአንቺ ደግሞ፣ ከአንቺ ጋር ከገባሁት የደም ቃል ኪዳን የተነሣ፣እስረኞችሽን ውሃ ከሌለበት ጒድጓድ ነጻ እለቃቸዋለሁ።