1 እናንተ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ልጆች ናችሁ፤ ለሞተ ሰው ሰውነታችሁን አትቦጭቁ፤ ከግንባራችሁ በላይ ያለውን ጠጒር አትላጩ፤
2 ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ ለራሱ የተለየ ሕዝብ እንድትሆንለት እግዚአብሔር (ያህዌ) በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ አንተን መርጦሃል።
3 ማናቸውንም ርኩስ ነገር አትብላ።
4 የምትበሏቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው፤ በሬ፣ በግ፣ ፍየል፣
5 ዋላ፣ ድኵላ፣ ሰስ፣ የበረሓ ፍየል፣ ዋሊያ፣ ሚዳቋ፣ አጋዘን።
6 ሰኰናው ስንጥቅ የሆነውን፣ ለሁለት የተከፈለውንና የሚያመሰኳ ማናቸውንም እንስሳ ብላ።
7 ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እንስሳት መካከል ግመልን፣ ጥንቸልንና ሽኮኮን አትብሉ፤ እነርሱ ቢያመሰኩ እንኳ፣ ሰኰናቸው የተሰነጠቀ ባለመሆኑ፣ በሥርዐቱ መሠረት በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።