ዘዳግም 33:13-19 NASV

13 ስለ ዮሴፍ ደግሞ እንዲህ አለው፦“እግዚአብሔር (ያህዌ) ምድሩን ይባርክ፤ድንቅ የሆነውን ጠል ከላይ ከሰማይ በማውረድ፣ከታች የተንጣለለውን ጥልቅ ውሃ በመስጠት፤

14 ፀሓይ በምታስገኘው ምርጥ ፍሬ፣ጨረቃም በምትሰጠው እጅግ መልካም ነገር፤

15 ከጥንት ተራሮች በተገኘ ምርጥ ስጦታ፣በዘላለማዊ ኰረብቶች ፍሬያማነት፤

16 ምድር በምታስገኘው ምርጥ ስጦታና በሙላቷ፣በሚቃጠለው ቊጥቋጦም ውስጥ በነበረው በእርሱ ሞገስ።እነዚህ ሁሉ በወንድሞቹ መካከል ገዥ በሆነው፣በዮሴፍ ዐናት ላይ ይውረዱ።

17 በግርማው እንደ በኵር ኰርማ ነው፤ቀንዶቹም የጐሽ ቀንዶች ናቸው።በእነርሱም ሕዝቦችን፣በምድር ዳርቻ ላይ ያሉትን እንኳ ሳይቀር ይወጋል፤እነርሱም የኤፍሬም ዐሥር ሺዎቹ ናቸው፤የምናሴም ሺዎቹ እንደዚሁ ናቸው።”

18 ስለ ዛብሎንም እንዲህ አለ፦“ዛብሎን ሆይ፤ ወደ ውጭ በመውጣትህ፣አንተም ይሳኮር በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ፤

19 አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤በዚያም የጽድቅን መሥዋዕት ያቀርባሉ።በባሕሮች ውስጥ ያለውን በተትረፈረፈ ብልጽግና፣በአሸዋውም ውስጥ የተደበቀውን ሀብት ይደሰቱበታል።”