ዘዳግም 33:9-15 NASV

9 ስለ አባቱና ስለ እናቱ ሲናገርም፣‘ስለ እነርሱ ግድ የለኝም’ አለ።ወንድሞቹን አልለያቸውም፤ልጆቹንም አላወቃቸውም።ለቃልህ ማን ጥንቃቄ አደረገ፤ኪዳንህንም ጠበቀ።

10 ሥርዐትህን ለያዕቆብ፣ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራል።ዕጣን በፊትህ፣የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ በመሠዊያህ ላይ ያቀርባል።

11 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ኀይሉን ሁሉ ባርክለት፤በእጁ ሥራ ደስ ይበልህ፤በእርሱ ላይ የሚነሡበትን ሽንጣቸውን ቊረጠው፤ጠላቶቹንም እንዳያንሠራሩ አድርገህ ምታቸው።”

12 ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦“የእግዚአብሔር (ያህዌ) ወዳጅ የሆነ በእርሱ ተጠብቆ በሰላም ይረፍ፤ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚወደውም ሰው በትከሻዎቹ መካከል ያርፋል።”

13 ስለ ዮሴፍ ደግሞ እንዲህ አለው፦“እግዚአብሔር (ያህዌ) ምድሩን ይባርክ፤ድንቅ የሆነውን ጠል ከላይ ከሰማይ በማውረድ፣ከታች የተንጣለለውን ጥልቅ ውሃ በመስጠት፤

14 ፀሓይ በምታስገኘው ምርጥ ፍሬ፣ጨረቃም በምትሰጠው እጅግ መልካም ነገር፤

15 ከጥንት ተራሮች በተገኘ ምርጥ ስጦታ፣በዘላለማዊ ኰረብቶች ፍሬያማነት፤