3 ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ብንያም፣
4 ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር።
5 የያዕቆብ ዘር ጠቅላላ ብዛት ሰባ ሲሆን፣ ዮሴፍ ግን ቀደም ብሎ በግብፅ ነበረ።
6 ከጊዜ በኋላ ዮሴፍና ወንድሞቹ ያም ትውልድ በሙሉ ሞቱ፤
7 ይሁን እንጂ እስራኤላውያን እየተዋለዱ በዙ፤ ቍጥራቸው እጅግ ከመጨመሩም የተነሣ የግብፅን ምድር ሞሏት።
8 በግብፅም፣ ስለ ዮሴፍ የማያውቅ አዲስ ንጉሥ ነገሠ።
9 እርሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፤ እስራኤላውያን በቍጥር በልጠውናል፤ ከእኛም ይልቅ እየበረቱ ነው፤