26 እንስሶቻችን ሁሉ አብረው መሄድ አለባቸው። አንድ ሰኰና እንኳን አይቀርም። ከእንስሶቻችን መካከል ለአምላካችን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) አምልኮ የምናቀርባቸው ይኖራሉ፤ ሆኖም እዚያ ከመድረሳችን በፊት እግዚአብሔርን (ያህዌ) ለማምለክ የምናቀርባቸው እንስሳት የትኞቹ እንደሆኑ አስቀድመን ለይተን ማወቅ አንችልም።”
27 ነገር ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ ፈርዖንም ሕዝቡን መልቀቅ አልፈቀደም።
28 ፈርዖን ሙሴን፣ “ከፊቴ ጥፋ! ስማ! ሁለተኛ እኔ ዘንድ እንዳትደርስ! ፊቴን ባየህበት በዚያ ቀን ፈጽመህ እንደምትሞት ዕወቅ” አለው።
29 ሙሴም፣ “እንዳልከው ይሁን! እኔም ዳግመኛ ከፊትህ አልደርስም” አለው።