16 “አንድ ሰው ያልታጨችን ልጃገረድ አታልሎ ክብረ ንጽሕናዋን ቢያጎድል፣ የማጫዋን ዋጋ ከፍሎ ሚስት ያድርጋት።
17 እርሷን ለእርሱ የልጅቷ አባት በሚስትነት ለመስጠት ከቶ የማይፈቅድ ቢሆን፣ ለድንግሎች መከፈል የሚገባውን ማጫ አሁንም ቢሆን መክፈል ይገባዋል።
18 “መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ።
19 “ከእንስሳ ጋር ሩካቤ ሥጋ የሚፈጽም ሰው ይገደል።
20 “ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በቀር ለሌላ አማልክት የሚሠዋ ይጥፋ።
21 መጻተኛውን አትበድሉት ወይም አታስጨንቁት፤ እናንተ በግብፅ መጻተኛ ነበራችሁና።
22 “ባል በሞተባት ወይም አባትና እናት በሌለው ልጅ ላይ ግፍ አትዋሉ።