1 የሐሰት ወሬ አትንዛ፤ ተንኰል ያለበትን ምስክርነት በመስጠት ክፉውን ሰው አታግዝ።
2 “ክፉ በማድረግ ብዙዎችን አትከተል፤ በሕግ ፊት ምስክርነት ስትሰጥ፣ ከብዙዎቹ ጋር ተባብረህ ፍትሕ አታጣምም።
3 በዳኝነት ጊዜ ለድኻው አታድላ።
4 “የጠላትህ በሬ ወይም አህያ ሲባዝን ብታገኘው ወደ እርሱ መልሰው።
5 የሚጠላህ ሰው አህያ፣ ጭነት ከብዶት ወድቆ ብታየው ርዳው እንጂ ትተኸው አትሂድ።
6 “በዳኝነት ጊዜ በድኻው ላይ ፍርድ አታጓድልበት።