1 ከዚያም ሙሴን “አንተና አሮን፣ ናዳብና አብድዩ ከሰባዎቹ የእስራኤል አለቆች ጋር ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ኑ፤ ከሩቅም ስገዱ አለው፤
2 ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሊቀርብ የሚችለው ሙሴ ብቻ ነው። ሌሎቹ መቅረብ የለባቸውም ሕዝቡም ከእርሱ ጋር መምጣት የለበትም።”
3 ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ቃሎችና ሕጎች ሁሉ በነገራቸው ጊዜ በአንድ ድምፅ ሆነው፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ሁሉ እናደርጋለን” አሉ።
4 ከዚያም ሙሴ እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ሁሉ ጻፈ። በማግሥቱም ማልዶ ተነሥቶ፣ በተራራው ግርጌ መሠዊያን ሠራ፤ አሥራ ሁለቱን የእስራኤልን ነገዶች የሚወክሉ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ።