1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አለው፤
2 “ስጦታ እንዲያመጡልኝ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። ይሰጥ ዘንድ ልቡ ካነሣሣው ከእያንዳንዱ ሰው ስጦታን ተቀበልልኝ።
3 ከእነርሱ የምትቀበላቸው ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ወርቅ፣ ብርና፣ ነሐስ፣
4 ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጒር፣
5 ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የለፋ ቆዳ፣ የግራር ዕንጨት፣
6 የመብራት ወይራ ዘይት፣ ለቅብዓ ዘይቱና ጣፋጭ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፣
7 በኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቍዎች።