24 በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።
25 ዙሪያውንም አንድ ስንዝር ስፋት ያለው ጠርዝ አብጅለት፤ በጠርዙም ዙሪያ የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።
26 ለጠረጴዛው አራት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ፣ አራቱ እግሮች ባሉበት በአራቱ ማእዘኖች ላይ አያይዘው።
27 ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች ይይዙ ዘንድ፣ ቀለበቶቹ ከክፈፉ አጠገብ ይሁኑ።
28 መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሥራቸው፤ በወርቅ ለብጣቸው፤ ጠረጴዛውንም ተሸከምባቸው።
29 ለመጠጥ ቍርባን መፍሰሻ ይሆኑም ዘንድ ዝርግ ሳሕኖችንና ወጭቶችን፣ እንዲሁም ማንቆርቆሪያዎቹንና ጎድጓዳ ሳሕኖቹን ከንጹሕ ወርቅ ሥራቸው።
30 በማንኛውም ጊዜ በፊቴ እንዲሆን ኅብስተ ገጹን በዚህ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጥ።