35 በመቅረዙ ላይ ላሉት ለስድስቱ ቅርንጫፎች እንቡጥ በመጀመሪያዎቹ ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር፣ ሁለተኛውም እንቡጥ በሁለተኛው ጥንድ ሥር፣ ሦስተኛውም እንቡጥ በሦስተኛው ጥንድ ሥር ይሁን።
36 ዕንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከመቅረዙ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ከንጹሕ ወርቅ ተቀርጸው ይሠሩ።
37 “ከዚያም ሰባት መብራቶች ሠርተህ ከመቅረዙ ፊት ለፊት ለሚገኘው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጡ ከመቅረዙ ላይ አስቀምጣቸው።
38 መኰስተሪያና የኵስታሪ ማስቀመጫ ሳህኖቹም ከንጹሕ ወርቅ ይሠሩ።
39 ለመቅረዙና ለዕቃዎቹ ሁሉ የሚያስፈልገው አንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ነው።
40 በተራራው ላይ ባሳየሁህ ዕቅድ መሠረት መሥራትህን ልብ በል።