12 ስለ ድንኳኑ መጋረጃዎች ትርፍ ቁመትም፣ ትርፍ ግማሽ መጋረጃ ከማደሪያው ድንኳን ጀርባ ላይ እንዲንጠለጠል ይሁን።
13 የድንኳኑ መጋረጃዎች በሁለቱም ጐኖች አንድ ክንድ ርዝመት ይኖራቸዋል፤ የተረፈውም የማደሪያውን ድንኳን ጎኖች እንዲሸፍን ሆኖ ይንጠለጠላል፤
14 ለድንኳኑ በቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ ልብስ አብጅ፤ በላዩም ላይ የአቆስጣ ቆዳ ይሁን።
15 “ለማደሪያው ድንኳን ከግራር ዕንጨት ወጋግራዎችን አብጅ።
16 እያንዳንዱም ወጋግራ ርዝመቱ ዐሥር ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ተኵል ይሁን፤
17 ሁለት ጉጦችም ጎን ለጎን ይሁኑለት፤ የማደሪያውን ድንኳን ወጋግራዎች ሁሉ በዚሁ መልክ አብጅ
18 ለማደሪያው ድንኳን ክፍል ሃያ ወጋግራዎችን ሥራ።