34 በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ በምስክሩ ታቦት ላይ የማስተስረያውን ክዳን አስቀምጥ።
35 ጠረጴዛውን ከመገናኛው ድንኳን በሰሜን በኩል ከመጋረጃው ውስጥ አስቀምጠው፤ መቅረዙንም ከእርሱ ትይዩ በማድረግ በደቡብ በኩል አድርገው።
36 “ለድንኳኑ ደጃፍ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ በጥልፍ ዐዋቂ የተጠለፈ መጋረጃ አብጅ።
37 ለዚህም መጋረጃ የወርቅ ኵላቦችንና ከግራር እንጨት የተሠሩ፣ በወርቅ የተለበጡ አምስት ምሰሶዎችን አብጅ፤ አምስት የናስ መቆሚያዎችንም አብጅላቸው።