ዘፀአት 4:1-7 NASV

1 ሙሴም “ባያምኑኝስ፤ ቃሌን ባይቀበሉስ፤ ‘እግዚአብሔር (ያህዌ) አልተገለጠልህም’ ቢሉኝስ?” ብሎ መለሰ።

2 እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “በእጅህ የያዝሀት እርሷ ምንድን ናት?” ሲል ጠየቀው፤ እርሱም መልሶ፣ “በትር ናት” አለው።

3 እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “መሬት ላይ ጣላት” አለው።ሙሴ በትሩን መሬት ላይ ጣላት፤ እባብም ሆነች፤ ከአጠገቧም ሸሸ።

4 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “በል እጅህን ዘርጋና ጅራቷን ያዛት” አለው። ሙሴም እጁን ዘርግቶ ሲይዛት እባቧ ተለውጣ በእጁ ላይ እንደ ገና በትር ሆነች።

5 እግዚአብሔርም (ያህዌ) “ይህ የሆነው የአባቶቻቸው አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር (ያህዌ) የተገለጠልህ መሆኑን እንዲያምኑ ነው” አለው።

6 እግዚአብሔርም (ያህዌ) ደግሞ፣ “እጅህን ብብትህ ውስጥ አስገባ” አለው። ሙሴም እጁን ብብቱ ውስጥ አስገባ፤ ከብብቱ ውስጥ ባወጣት ጊዜ እጁ እንደ በረዶ ለምጽ ሆነች።

7 “አሁንም ደግሞ እጅህን ወደ ብብትህ መልሰህ አስገባ” አለው። ሙሴም እጁን መልሶ ብብቱ ውስጥ አስገባ፤ እንደ ገና እጁን ከብብቱ ውስጥ ባወጣት ጊዜ፣ ተመልሳ እንደ ሌላው የሰውነቱ ክፍል ሆነች።