21 ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው ታቦቱን ወደ ማደሪያው ድንኳን አስገብቶ መከለያ መጋረጃውን ሰቀለ፤ የምስክሩንም ታቦት ጋረደው።
22 ሙሴ ጠረጴዛውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣ ከማደሪያው በስተ ሰሜን ከመጋረጃው ውጭ አኖረው፤
23 እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘውም ኅብስቱን በላዩ ላይ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አኖረ።
24 መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከጠረጴዛው ትይዩ ከማደሪያው ድንኳን በስተ ደቡብ በኩል አኖረው፤
25 እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘውም መብራቶቹን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አበራ።
26 ሙሴ የወርቅ መሠዊያውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ፊት ለፊት አኖረው፤
27 እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘውም መልካም መዐዛ ያለውን ዕጣን አጠነበት።