20 እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ናቸው።
21 ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔ ቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው።
22 የሴም ልጆች፦ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።
23 የአራም ልጆች፦ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ ናቸው።
24 አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ሳላም ዔቦርን ወለደ።
25 ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፍሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።
26 ዮቅጣንም፦ የኤልሞሳድ፣ የሣሌፍ፣ የሐስረ ሞት፣ የያራሕ፣