ዘፍጥረት 18:26-32 NASV

26 እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “በሰዶም ከተማ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ለእነርሱ ስል አገሪቱን በሞላ እምራለሁ” አለ።

27 ደግሞም አብርሃም እንዲህ አለ፤ “እኔ ከንቱ፣ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታ (አዶናይ) ጋር ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤

28 ለመሆኑ ከአምሳው ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ በአምስቱ ሰዎች ምክንያት መላ ከተማዋን ታጠፋለህን?”እርሱም፣ “አርባ አምስት ጻድቃን ባገኝ አላጠፋትም” አለ።

29 አብርሃምም እንደ ገና፣ “ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?” አለ እርሱም፣ “ለአርባው ስል እምራታለሁ” አለ።

30 ደግሞም አብርሃም፣ “ጌታዬ (አዶናይ) አይቈጣ፤ እባክህ ልናገር፤ ሠላሳ ጻድቃን ብቻ ቢገኙስ?”እርሱም፣ “ሠላሳ ባገኝ አላጠፋትም” ብሎ መለሰ።

31 አብርሃምም፣ “ከጌታ (አዶናይ) ጋር እናገር ዘንድ መቼም አንዴ ደፍሬአለሁና ምናልባት ሃያ ብቻ ቢገኙስ?” አለ።እርሱም፣ “ሃያ ቢገኙ፣ ለእነርሱ ስል እምራታለሁ” አለ።

32 አብርሃምም፣ “ጌታዬ (አዶናይ) አይቈጣ፤ አንድ ጊዜ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት ዐሥር ብቻ ቢገኙስ?” አለ።እርሱም “ስለ ዐሥሩ ስል አላጠፋትም” ብሎ መለሰ።