11 እንደ ገናም፣“አሕዛብም ሁላችሁ ጌታን አመስግኑ፤ሕዝቦች ሁሉ ወድሱት” ይላል።
12 ኢሳይያስም እንዲሁ፣“በሕዝቦች ሁሉ ላይ የሚነግሠው፣የእሴይ ሥር ይመጣል፤በእርሱም አሕዛብ ተስፋ ያደርጋሉ” ይላል።
13 በእርሱ በመታመናችሁ የተስፋ አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፤ ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተስፋ ተትረፍርፎ እንዲፈስላችሁ ነው።
14 ወንድሞቼ ሆይ፤ እናንተ ራሳችሁ በበጎነት የተሞላችሁ፣ በዕውቀት ሁሉ እንደ ተሞላችሁና አንዱ ሌላውን ለመምከር ችሎታ ያላችሁ መሆናችሁን እኔ ራሴ ርግጠኛ ሆኜ አለሁ።
15 እግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መሠረት፣ እንደ ገና ዐሳስባችሁ ዘንድ በአንዳንድ ጒዳዮች ላይ በድፍረት የጻፍሁላችሁ፣
16 በእግዚአብሔር ወንጌል የክህነት ተግባር፣ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ ለመሆን ነው፤ ይኸውም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው።
17 ስለዚህ እግዚአብሔርን በማገልገሌ በክርስቶስ ኢየሱስ እመካለሁ።