7 እንግዲህ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሆን ዘንድ ክርስቶስ እንደተቀበላችሁ፣ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ።
8 ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ ለእግዚአብሔር እውነት ሲል ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ እንደሆነ እነግራችኋለሁና፤
9 እንዲሁም አሕዛብ እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ ያመሰግኑት ዘንድ ነው፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤“ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ለስምህም እዘምራለሁ።”
10 ደግሞም፣“አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ” ይላል።
11 እንደ ገናም፣“አሕዛብም ሁላችሁ ጌታን አመስግኑ፤ሕዝቦች ሁሉ ወድሱት” ይላል።
12 ኢሳይያስም እንዲሁ፣“በሕዝቦች ሁሉ ላይ የሚነግሠው፣የእሴይ ሥር ይመጣል፤በእርሱም አሕዛብ ተስፋ ያደርጋሉ” ይላል።
13 በእርሱ በመታመናችሁ የተስፋ አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፤ ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተስፋ ተትረፍርፎ እንዲፈስላችሁ ነው።