1 ስለዚህ አንተ በሌላው ላይ የምትፈርድ፣ የምታመካኝበት የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር ሁሉ፣ ራስህን ትኰንናለህ፤ ፈራጅ የሆንኸው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።
2 እንደዚህ በሚያደርጉትም ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ ትክክለኛ መሆኑን እናውቃለን።
3 እንግዲህ አንተ ሰው በሌሎች ላይ እየፈረድህ፣ ያንኑ የምታደርግ ከሆነ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃል?
4 ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሓ የሚመራህ መሆኑን ሳትገነዘብ፣ የቸርነቱን፣ የቻይነቱን የትዕግሥቱን ባለጠግነት ትንቃለህ?
5 ነገር ግን በድንዳኔህና ንስሓ በማይገባ ልብህ ምክንያት ትክክለኛ ፍርዱ ሲገለጥ በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን በራስህ ላይ ቊጣን ታከማቻለህ።
6 እግዚአብሔር “ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል”፤