2 ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።
3 እግዚአብሔር ጻድቁ እንዲራብ አያደርግም፤የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል።
4 ሰነፍ እጆች ሰውን ያደኸያሉ፤ትጉ እጆች ግን ብልጽግናን ያመጣሉ።
5 ሰብሉን በበጋ የሚሰበስብ ጠቢብ ልጅ ነው፤በመከር ጊዜ የሚተኛ ግን ውርደት ይከተለዋል።
6 በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው፤መዓት ግን የክፉዎችን አፍ ይዘጋል።
7 የጻድቃን መታሰቢያቸው በረከት ነው፤የክፉዎች ስም ግን እንደ ጠፋ ይቀራል።
8 በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝ ይቀበላል፤ለፍላፊ ተላላ ግን ወደ ጥፋት ያመራል።