7 ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው ከንቱ ትሆናለች፤በኀይሉ የተመካበትም ሁሉ እንዳልነበረ ይሆናል።
8 ጻድቅ ከመከራ ይድናል፤ይልቁን መከራው በክፉው ላይ ይደርሳል።
9 ክፉ ሰው ባልንጀራውን በአፉ ያጠፋል፤ጻድቃን ግን በዕውቀት ያመልጣሉ።
10 ጻድቃን ሲሳካላቸው ከተማ ደስ ይላታል፤ክፉዎች ሲጠፉ እልልታ ይሆናል።
11 በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤በክፉዎች አንደበት ግን ትጠፋለች።
12 ማመዛዘን የጐደለው ሰው ባልንጀራውን ያንኳስሳል፤አስተዋይ ግን አንደበቱን ይገዛል።
13 ሐሜተኛ ምስጢር አይጠብቅም፤ታማኝ ሰው ግን ምስጢር ይጠብቃል።