10 ጻድቅ ሰው ለእንስሳቱ ይራራል፤ክፉዎች ራሩ ቢባል እንኳ ዞሮ ዞሮ ሥራቸው ጭካኔ ነው።
11 መሬቱን የሚያርስ የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ከንቱ ተስፋን የሚያሳድድ ግን ማመዛዘን ይጐድለዋል።
12 ኀጥኣን የክፉዎችን ምርኮ ይመኛሉ፤የጻድቅ ሥር ግን ይንሰራፋል።
13 ክፉ ሰው በእኩይ ንግግሩ ይጠመዳል፤ጻድቅ ሰው ግን ከመከራ ያመልጣል።
14 ሰው ከከንፈሩ ፍሬ የተነሣ በበጎ ነገር ይሞላል፤እንደ እጁ ሥራም ተገቢውን ዋጋ ያገኛል።
15 ተላላ ሰው መንገዱ ትክክል መስሎ ይታየዋል፤ጠቢብ ሰው ግን ምክር ይሰማል።
16 ተላላ ሰው ቊጣው ወዲያውኑ ይታወቅበታል፤አስተዋይ ሰው ግን ስድብን ንቆ ይተዋል።