6 ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።
7 ባለጠጋ ድኻን ይገዛል፤ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው።
8 ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፤የቊጣውም በትር ይጠፋል።
9 ቸር ሰው ራሱ ይባረካል፤ምግቡን ከድኾች ጋር ይካፈላልና።
10 ፌዘኛን አስወጣው፤ ጠብ ይወገዳል፤ጥልና ስድብም ያከትማል።
11 የልብ ንጽሕናን ለሚወድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።
12 የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤የማይታመኑትን ሰዎች ቃል ግን እርሱ ከንቱ ያደርጋል።