3 በዚያም በምዕራብ በኩል ቊልቊል ወደ የፍሌጣውያን ግዛት እስከታችኛው ቤትሖሮን ምድር ይወርድና ወደ ጌዝር ዘልቆ ባሕሩ ላይ ይቆማል።
4 ስለዚህ የዮሴፍ ዘሮች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ተቀበሉ።
5 ለኤፍሬም ወገን በየጐሣ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ድርሻ ይህ ነው፤ድንበሩ በምሥራቅ በኩል ከአጣሮት አዳር ተነሥቶ እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ይወጣና፣
6 እስከ ባሕሩ ይዘልቃል። በስተ ሰሜን ደግሞ ከሚክምታት ተነሥቶ በምሥራቅ በኩል ወደ ተአናት ሴሎ ይታጠፍና ከዚያ በማለፍ እስከ ኢያኖክ ምሥራቅ ይዘልቃል፤
7 ከኢያኖክም በመነሣት ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ቊልቊል ይወርድና በኢያሪኮ በኩል አድርጎ ዮርዳኖስ ላይ ብቅ ይላል።
8 ድንበሩ አሁንም ከታጱዋ በምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ቃና ወንዝ ይወርድና ከባሕሩ ላይ ይቆማል። እንግዲህ የኤፍሬም ነገድ በየጐሣ በየጐሣቸው የተካፈሉት ርስት ይህ ነበር።
9 ይህም በምናሴ ነገድ ርስት ውስጥ ለኤፍሬም ዘሮች የተመደቡትን ከተሞች በሙሉና መንደሮቻቸውን የሚያጠቃልል ነው።