ዘፀአት 37:19-25 NASV

19 ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች በአንዱ ቅርንጫፍ ላይ፣ ሦስቱ ደግሞ በሚቀጥለው ቅርንጫፍ ላይ ነበሩ፤ ከመቅረዙ ለወጡት ለስድስቱም ቅርንጫፎች ሁሉ እንዲሁ ነበር።

20 እንቡጦችና የፈኩ አበቦች ያሉባቸው የለውዝ አበባ የሚመስሉ አራት ጽዋዎች በመቅረዙ ላይ ነበሩ።

21 አንደኛው እንቡጥ ከመቅረዙ ወጣ ብለው በሚገኙት በመጀመሪያው ጥንድ ቅርንጫፎች ሥር ሁለተኛውም እምቡጥ በሁለተኛው ጥንድ ሥር እንዲሁም ሦስተኛው እንቡጥ በሦስተኛው ጥንድ ሥር ነበር፣ በስድስቱም ቅርንጫፎች እንዲሁ ነበር።

22 እንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ ተሠርተው ከመቅረዙ ጋር አንድ ወጥ ነበሩ።

23 የመቅረዙን ሰባት መብራቶች፣ እንዲሁም መኮስተሪያዎችንና የኵስታሪ ማስቀ መጫዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ።

24 መቅረዙንና ዕቃዎቹን ሁሉ ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ሠሩ።

25 የዕጣን መሠዊያውን ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ ርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱ፣ አንድ ክንድ፣ ከፍታው ሁለት ክንድ ነበር፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ተሠርተው ነበር።