13 ቤንጌበር፣ በገለዓድ ራሞት ከተማእዚያው ገለዓድ ውስጥ የምናሴልጅ የኢያዕር መንደሮች፣ በባሳንምየአርጎብ አውራጃ እንዲሁም በሮቻቸው የናስ መወርወሪያ በሆኑ ሥልሳባለ ቅጥር ታላላቅ ከተሞች፤
14 የዒዶ ልጅ አሒናዳብ፤ በማሃናይም፣
15 አኪማአስ በንፍታሌም፣ እርሱምየሰሎሞንን ልጅ ባስማትን አግብቶየነበረ ነው፤
16 የኩሲ ልጅ በዓና፤ በአሴርና በበዓሎት፣
17 የፋሩዋ ልጅ ኢዮሣፍጥ በይሳኮር፣
18 የኤላ ልጅ ሳሚ በብንያም፣
19 የኡሪ ልጅ ጌበር፤በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣በባሳን ንጉሥ በዐግ አገር፣ እርሱምየአውራጃው ብቸኛ ገዥ ነበር።