47 ሰሎሞን ከብዛታቸው የተነሣ እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች እንዲመዘኑ አላደረገም፣ ስለዚህም የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበረ አልታወቀም።
48 እንዲሁም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አግልግሎት እንዲውሉ ከዚህ የሚከተሉትን ዕቃዎች ሁሉ ሠራ፤የወርቅ መሠዊያን፣ገጸ ኅብስቱ የሚቀመጥበትን የወርቅ ጠረጴዛ፤
49 በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በቀኝ፣ አምስቱ በግራ የሚቀመጡ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞችን፣ ከወርቅ የተሠሩአበቦችን፣ የመብራት ቀንዲሎችንና መቈስቈሻዎችን፤
50 የንጹሕ ወርቅ ሳሕኖችን፣ የመብራት መኰስተሪያዎችን፣ ለመርጫ የሚሆኑ ጐድጓዳ ሳሕኖችንና ጭልፋዎችን፣የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎችን፣ ለውስጠኛው ክፍል ለቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ በሮች የሚሆኑ የወርቅ ማጠፊያዎችን።
51 ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር የለየውን ብሩንና ወርቁን እንዲሁም ዕቃውን አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አኖረ።