1 ነገሥት 1:19-25 NASV

19 እርሱ በሬዎችን፣ ኮርማዎችንና በጎችን በብዛት ሠውቶአል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ ካህኑን አብያታርንና የሰራዊቱን አዛዥ ኢዮአብን ጠርቶአል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጠራውም።

20 ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ከአንተ ቀጥሎ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ ማን መቀመጥ እንዳለበት እንድታሳውቀው የእስራኤል ዐይን ሁሉ አንተን ይመለከታል።

21 ያለበለዚያ ግን ንጉሥ ጌታዬ ከአባቶቹ ጋር በሚያንቀላፋበት ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎሞን እንደ ወንጀለኞች እንቈጠራለን።”

22 እርሷ ከንጉሡ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለች ነቢዩ ናታን ገባ።

23 ለንጉሡም፣ “ነቢዩ ናታን መጥቶአል” ብለው ነገሩት፤ እርሱም ንጉሡ ፊት ቀርቦ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ።

24 ናታንም እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ለመሆኑ አዶንያስ ከአንተ ቀጥሎ እንደሚነግሥ፣ በዙፋንህም እንደሚቀመጥ አስታውቀሃልን?

25 በዛሬው ቀን ታች ወርዶ ብዙ በሬዎች፣ ኮርማዎችና በጎች ሠውቶአል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ የሰራዊቱን አዛዦችና ካህኑን አብያታርንም ጠርቶአል፤ እነሆ፤ አሁን፣ ‘አዶንያስ ለዘላለም ይኑር’ እያሉ ከእርሱ ጋር በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው።