49 በዚህም አዶንያስና የጠራቸው እንግዶች በሙሉ ደንግጠው ተነሡ፤ በየአቅጣጫውም ተበታተኑ።
50 አዶንያስ ግን ሰሎሞንን በመፍራት ሄዶ፣ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ።
51 ከዚያም፣ ለሰሎሞን፣ “አዶንያስ እነሆ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በመፍራት የመሠዊያውን ቀንድ ይዞ ተማጥኖአል፤ እርሱም፣ ‘ባሪያውን በሰይፍ እንዳይገድለው ንጉሡ ሰሎሞን ዛሬውኑ ይማልልኝ’ ብሎአል” ብለው ነገሩት።
52 ሰሎሞንም፣ “አካሄዱን ካሳመረ ከራስ ጠጒሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም፤ ጥፋት ከተገኘበት ግን ይሞታል” ሲል መለሰ።
53 ከዚያም ንጉሥ ሰሎሞን ሰዎች ልኮ ከመሠዊያው ላይ አወረዱት። አዶንያስም መጥቶ ለንጉሥ ሰሎሞን አጐንብሶ እጅ ነሣ፤ ሰሎሞንም፣ “በል ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።