1 ነገሥት 7:34-40 NASV

34 እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ወጣ ያለ እጀታ ነበረው።

35 በዕቃ ማስቀመጫው ጫፍ ላይ ግማሽ ክንድ የሆነ ዙሪያ ክብ ነበረበት፤ ድጋፎቹና ጠፍጣፋ ናሶቹ ከዕቃ ማስቀመጫው አናት ጋር የተያያዙ ነበሩ።

36 እርሱም በድጋፎቹና በጠፍጣፋ ናሶቹ ላይ ባለው ቦታ ሁሉ፣ ዙሪያውን የአበባ ጒንጒን እያደረገ ኪሩቤልን፣ አንበሶችንና የዘንባባ ዛፎችን ቀረጸ።

37 ዐሥሩም የዕቃ ተሸካሚዎች የተሠሩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ሁሉም ከአንድ ቅርጽ ቀልጠው የወጡ ስለ ሆነ፣ በመጠንና በቅርጽ ፍጹም ተመሳሳይ ነበሩ።

38 ከዚያም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ የሚሆን፣ እያንዳንዱ ስምንት መቶ ሰማንያ ሊትር የሚይዝ ዐሥር የናስ መታጠቢያ ገንዳ ሠራ፤ ስፋቱም አራት ክንድ ነበር።

39 ከዕቃ ማስቀመጫዎቹም አምስቱን ከመቅደሱ በስተ ደቡብ፣ አምስቱን በስተ ሰሜን በኩል አኖረ፤ ገንዳውንም ከቤተ መቅደሱ በደቡብ ምሥራቅ ጫፍ ላይ በስተ ደቡብ አኖረው።

40 እንዲሁም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችንና ድስቶችን ሠራ፤ኪራምም በዚህ ሁኔታ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ እንደሚከተለው ፈጸመ፤