1 ነገሥት 9:21-27 NASV

21 እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን እነዚህን እስከ ዛሬ እንደሚደረገው ሁሉ፣ ሰሎሞን ለግዳጅ ሥራ መለመላቸው።

22 ይሁን እንጂ ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ማንንም ባሪያ አላደረገም፤ እነርሱ ወታደሮቹ፣ ሹማምቱ፣ የጦር አለቆቹ፣ ሻምበሎቹ፣ ባልደራሶቹ ነበሩ።

23 እነዚህም ሰሎሞን የሚያሠራውን የሕንጻ ሥራ የሚያከናውኑትን ሠራተኞች የሚቈጣጠሩ ናቸው፤ ቍጥራቸውም አምስት መቶ አምሳ ነበር።

24 የፈርዖን ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከመጣች በኋላ ሰሎሞን ሚሎንን ሠራ።

25 ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ባሠራው መሠዊያ ላይ በዓመት ሦስት ጊዜ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በማቅረብ፣ ከዚሁ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም የቤተ መቅደሱን ግዳጅ ተወጣ።

26 እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን በኤዶምያስ ምድር፣ በኤሎት አጠገብ፣ በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ።

27 በመርከቦቹም ላይ ከሰሎሞን ሰዎች ጋር አብረው እንዲሠሩ፣ ኪራም ባሕሩን የሚያውቁ የራሱን መርከበኞች ላከ።