24 የፈርዖን ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከመጣች በኋላ ሰሎሞን ሚሎንን ሠራ።
25 ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ባሠራው መሠዊያ ላይ በዓመት ሦስት ጊዜ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በማቅረብ፣ ከዚሁ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም የቤተ መቅደሱን ግዳጅ ተወጣ።
26 እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን በኤዶምያስ ምድር፣ በኤሎት አጠገብ፣ በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ።
27 በመርከቦቹም ላይ ከሰሎሞን ሰዎች ጋር አብረው እንዲሠሩ፣ ኪራም ባሕሩን የሚያውቁ የራሱን መርከበኞች ላከ።
28 እነዚያም ወደ ኦፊር ሄደው አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ይዘው ተመለሱ፤ ይህንም ለንጉሥ ሰሎሞን ሰጡት።