መሳፍንት 9:12-18 NASV

12 “ከዚያም ዛፎቹ የወይን ተክልን፣ ‘መጥተህ ንጉሣችን ሁን’ አሉት።

13 “የወይን ተክሉም፣ ‘ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፣ አማልክትንና ሰዎችን ደስ የሚያሰኘውን የወይን ጠጄን መስጠት ልተውን? አለ።

14 በመጨረሻም ዛፎቹ በሙሉ የእሾኽ ቊጥቋጦን፣ ‘መጥተህ ንጉሣችን ሁን’ አሉት።

15 “የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፣ ‘በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾኽ ቊጥቋጦው ይነሣ! የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ’ አላቸው።

16 “እንግዲህ አቤሜሌክን ስታነግሡት በቅንነትና በእውነት አድርጋችሁት ከሆነ፣ ይሩበኣልንና ቤተ ሰቡን በበጎ ዐይን ተመልክታችሁ ላደረገው የሚገባውን አይታችሁለት ከሆነ፣

17 አባቴ ለእናንተ መዋጋቱን፣ ከምድያማውያን እጅ ሊያድናችሁ ሕይወቱን መስጠቱን አሰባችሁ ማለት ነው።

18 ነገር ግን እናንተ ዛሬ በአባቴ ቤተ ሰብ ላይ ዐመፃችሁ፤ ሰባ ልጆቹን በአንዲት ድንጋይ ላይ ዐረዳችሁ፤ ዘመዳችሁ ስለ ሆነም አባቴ ከባሪያው የወለደውን ልጅ አቤሜሌክን በሴኬም ነዋሪዎች ላይ አነገሣችሁት።