Bible
Now
Toggle navigation
ምዕራፎች
1
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
መጽሐፍት
ብሉይ ኪዳን
ዘፍጥረት
ዘፀአት
ዘሌዋውያን
ዘኁልቍ
ዘዳግም
ኢያሱ
መሳፍንት
ሩት
1 ሳሙኤል
2 ሳሙኤል
1 ነገሥት
2 ነገሥት
1 ዜና መዋዕል
2 ዜና መዋዕል
ዕዝራ
ነህምያ
አስቴር
ኢዮብ
መዝሙር
ምሳሌ
መክብብ
ማሕልየ መሓልይ
ኢሳይያስ
ኤርምያስ
ሰቆቃወ
ሕዝቅኤል
ዳንኤል
ሆሴዕ
ኢዩኤል
አሞጽ
አብድዩ
ዮናስ
ሚክያስ
ናሆም
ዕንባቆም
ሶፎንያስ
ሐጌ
ዘካርያስ
ሚልክያስ
አዲስ ኪዳን
ማቴዎስ
ማርቆስ
ሉቃስ
ዮሐንስ
ሐዋርያት ሥራ
ሮሜ
1 ቆሮንቶስ
2 ቆሮንቶስ
ገላትያ
ኤፌሶን
ፊልጵስዩስ
ቈላስይስ
1 ተሰሎንቄ
2 ተሰሎንቄ
1 ጢሞቴዎስ
2 ጢሞቴዎስ
ቲቶ
ፊልሞና
ዕብራውያን
ያዕቆብ
1 ጴጥሮስ
2 ጴጥሮስ
1 ዮሐንስ
2 ዮሐንስ
3 ዮሐንስ
ይሁዳ
ራእይ
መጽሐፍ ዝርዝር
NASV
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
AM
Afrikaans (AF)
Avañe’ẽ (GN)
Bahasa Indonesia (ID)
Bahasa Melayu (MS)
Basa Jawa (JV)
Bokmål (NB)
Català (CA)
ChiCheŵa (NY)
ChiShona (SN)
Cymraeg (CY)
Dansk (DA)
Deutsch (DE)
Eesti (ET)
English (EN)
Español (ES)
Euskara (EU)
Français (FR)
Gaeilge (GA)
Gagana fa’a Sāmoa (SM)
Hausa (HA)
Hrvatski (HR)
Igbo (IG)
IsiXhosa (XH)
IsiZulu (ZU)
Italiano (IT)
Kiswahili (SW)
Latine (LA)
Latviešu (LV)
Lietuvių (LT)
Magyar (HU)
Malagasy (MG)
Nederlands (NL)
Nynorsk (NN)
Polski (PL)
Português (PT)
Română (RO)
Sesotho (ST)
Shqip (SQ)
Slovenčina (SK)
Slovenščina (SL)
Soomaali (SO)
Suomi (FI)
Svenska (SV)
Tagalog (TL)
Cebuano (CEB)
Tiếng Việt (VI)
Türkçe (TR)
Èdè Yorùbá (YO)
čeština (CS)
Ελληνικά (EL)
Српски (SR)
български (BG)
македонски (MK)
монгол (MN)
русский (RU)
українська (UK)
Հայերէն (HY)
עברית (HE)
اردو (UR)
العربية (AR)
سنڌي (SD)
فارسی (FA)
हिन्दी (HI)
বাংলা (BN)
தமிழ் (TA)
ไทย (TH)
မြန်မာဘာသာ (MY)
አማርኛ (AM)
ភាសាខ្មែរ (KM)
日本語 (JA)
简体中文 (ZH)
繁體中文 (ZH-HANT)
한국어 (KO)
☽
Enable dark mode
ምዕራፎች
1
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
መጽሐፍት
ብሉይ ኪዳን
ዘፍጥረት
ዘፀአት
ዘሌዋውያን
ዘኁልቍ
ዘዳግም
ኢያሱ
መሳፍንት
ሩት
1 ሳሙኤል
2 ሳሙኤል
1 ነገሥት
2 ነገሥት
1 ዜና መዋዕል
2 ዜና መዋዕል
ዕዝራ
ነህምያ
አስቴር
ኢዮብ
መዝሙር
ምሳሌ
መክብብ
ማሕልየ መሓልይ
ኢሳይያስ
ኤርምያስ
ሰቆቃወ
ሕዝቅኤል
ዳንኤል
ሆሴዕ
ኢዩኤል
አሞጽ
አብድዩ
ዮናስ
ሚክያስ
ናሆም
ዕንባቆም
ሶፎንያስ
ሐጌ
ዘካርያስ
ሚልክያስ
አዲስ ኪዳን
ማቴዎስ
ማርቆስ
ሉቃስ
ዮሐንስ
ሐዋርያት ሥራ
ሮሜ
1 ቆሮንቶስ
2 ቆሮንቶስ
ገላትያ
ኤፌሶን
ፊልጵስዩስ
ቈላስይስ
1 ተሰሎንቄ
2 ተሰሎንቄ
1 ጢሞቴዎስ
2 ጢሞቴዎስ
ቲቶ
ፊልሞና
ዕብራውያን
ያዕቆብ
1 ጴጥሮስ
2 ጴጥሮስ
1 ዮሐንስ
2 ዮሐንስ
3 ዮሐንስ
ይሁዳ
ራእይ
መጽሐፍ ዝርዝር
NASV
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
AM
Afrikaans (AF)
Avañe’ẽ (GN)
Bahasa Indonesia (ID)
Bahasa Melayu (MS)
Basa Jawa (JV)
Bokmål (NB)
Català (CA)
ChiCheŵa (NY)
ChiShona (SN)
Cymraeg (CY)
Dansk (DA)
Deutsch (DE)
Eesti (ET)
English (EN)
Español (ES)
Euskara (EU)
Français (FR)
Gaeilge (GA)
Gagana fa’a Sāmoa (SM)
Hausa (HA)
Hrvatski (HR)
Igbo (IG)
IsiXhosa (XH)
IsiZulu (ZU)
Italiano (IT)
Kiswahili (SW)
Latine (LA)
Latviešu (LV)
Lietuvių (LT)
Magyar (HU)
Malagasy (MG)
Nederlands (NL)
Nynorsk (NN)
Polski (PL)
Português (PT)
Română (RO)
Sesotho (ST)
Shqip (SQ)
Slovenčina (SK)
Slovenščina (SL)
Soomaali (SO)
Suomi (FI)
Svenska (SV)
Tagalog (TL)
Cebuano (CEB)
Tiếng Việt (VI)
Türkçe (TR)
Èdè Yorùbá (YO)
čeština (CS)
Ελληνικά (EL)
Српски (SR)
български (BG)
македонски (MK)
монгол (MN)
русский (RU)
українська (UK)
Հայերէն (HY)
עברית (HE)
اردو (UR)
العربية (AR)
سنڌي (SD)
فارسی (FA)
हिन्दी (HI)
বাংলা (BN)
தமிழ் (TA)
ไทย (TH)
မြန်မာဘာသာ (MY)
አማርኛ (AM)
ភាសាខ្មែរ (KM)
日本語 (JA)
简体中文 (ZH)
繁體中文 (ZH-HANT)
한국어 (KO)
☽ Dark mode
›
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
›
ብሉይ ኪዳን
›
መሳፍንት
›
መሳፍንት 1
መሳፍንት
ምዕራፎች 1
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ኢያሱ 24
መሳፍንት 2
እስራኤላውያን ከቀሩት ከነዓናውያን ጋር ያደረጉት ውጊያ
1
ኢያሱ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን፣ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ማን ቀድሞ ይውጣልን?” ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ።
2
እግዚአብሔርም፣ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ፤ እነሆ ምድሪቱን በእጁ አሳልፌ ሰጥቼዋለሁ” በማለት መለሰ።
3
የይሁዳም ሰዎች ወንድሞቻቸውን የስምዖንን ልጆች፣ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ድርሻችን ወደ ሆነው ምድር አብረን እንውጣ፤ እኛም እንደዚሁ ድርሻችሁ ወደ ሆነው ምድር አብረናችሁ እንወጣለን” አሏቸው፤ ስለዚህም የስምዖን ሰዎች አብረዋቸው ሄዱ።
4
ይሁዳ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ላይ ወጣ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ ቤዜቅ በተባለውም ስፍራ ዐሥር ሺህ ሰው ገደሉ።
5
በዚህም ኦዶኒቤዜቅን አግኝተው ተዋጉት፤ ከነዓናውያንንና ፌርዛውያንን ድል አደረጉ።
6
አዶኒቤዜቅም ከዚያ ሸሸ፤ እነርሱ ግን አሳደው ያዙት፤ የእጆቹንና የእግሮቹንም አውራ ጣቶች ቈረጡ።
7
ከዚያም አዶኒቤዜቅ፣ “የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር የወደቀ ፍርፋሪ ይለቃቅሙ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የፈጸምሁትን አመጣብኝ” አለ፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ በዚያም ሞተ።
8
የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ወግተው ያዟት፤ ከተማዪቱንም በሰይፍ ስለት መተው፣ በእሳት አቃጠሏት።
9
ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሰዎች በኰረብታማው አገር፣ በኔጌብና በምዕራቡ ኮረብታ ግርጌ የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ለመውጋት ወረዱ፤
10
ቀደም ሲል ቂርያት አርባቅ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን በሚኖሩት ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ሴሲንን፣ አኪመንንና ተላሚንን ድል አደረጉ።
11
ከዚያም ቀደም ሲል ቅርያትሤፍር ተብላ በምትጠራው በዳቤር በሚኖሩት ሰዎች ላይ ዘመቱ።
12
ካሌብም፣ “ቅርያት ሤፍርን ወግቶ ለሚይዛት ሰው ልጄን ዓክሳንን እድርለታለሁ” አለ።
13
በዚህ ጊዜ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዘ፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳንን ዳረለት።
14
እርሷም ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜ፣ አባቷ የዕርሻ መሬት እንዲሰጠው ይለምነው ዘንድ አጥብቃ ነገረችው፤ ካሌብም እርሷ ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት።
15
እርሷም፣ “እባክህ አንድ ነገር አድርግልኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።
16
የቄናዊው የሙሴ ዐማት ዝርያዎች ከዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋር አብረው ለመኖር፣ ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከባለ ዘንባባዋ ከተማ ከኢያሪኮ ወጡ።
17
የይሁዳ ሰዎች ከወንድሞቻቸው ከስምዖን ልጆች ጋር ሆነው በጻፋት በሚኖሩት ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ከተማዪቱንም ፈጽሞ ደመሰሷት፤ ስለዚህ ከተማዪቱ ሔርማ ተብላ ተጠራች።
18
ደግሞም የይሁዳ ሰዎች ጋዛ፣ አስቀሎና፣ አቃሮን የተባሉትን ከተሞች ከነግዛቶቻቸው ያዙ።
19
እግዚአብሔር ከይሁዳ ሰዎች ጋር ነበር፤ ስለዚህ ኰረብታማውን አገር ያዙ፤ ነገር ግን በረባዳው ምድር የሚኖሩት ሰዎች ከብረት የተሠሩ ሠረገሎች ስለ ነበሯቸው ከዚያ አሳደው ሊያስወጧቸው አልቻሉም።
20
ሙሴ ባዘዘው መሠረት ኬብሮን ለካሌብ ተሰጠች፤ እርሱም ሦስቱን የዔናቅ ልጆች ከውስጧ አሳደደ።
21
የብንያም ልጆች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ከዚያ ሊያስወጧቸው አልቻሉም፤ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከብንያማውያንጋር በዚያ አብረው ይኖራሉ።
22
የዮሴፍ ወገን ደግሞ ቤቴልን ወጉ፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነበር።
23
እነርሱም ቀደም ሲል ሎዛ ትባል ወደ ነበረችው ወደ ቤቴል ሰላዮችን በላኩ ጊዜ፣
24
ሰላዮቹም አንድ ሰው ከከተማዪቱ ሲወጣ አይተው፤ “የከተማዪቱን መግቢያ አሳየን፤ እኛም ምሕረት እናደርግልሃለን” አሉት።
25
እርሱም አሳያቸው፤ እነርሱም ከሰውየውና ከቤተ ሰቡ በስተቀር የከተማዪቱን ሕዝብ በሰይፍ ስለት ፈጁ።
26
ሰውየውም ወደ ኬጢያውያን ምድር ሄዶ ከተማ ሠራ፤ ስሟንም ሎዛ ብሎ ጠራት፤ እስከ ዛሬም የምትጠራው በዚሁ ስም ነው።
27
የምናሴ ነገድ ግን በቤትሳን፣ በታዕናክ፣ በዶር፣ በይብለዓም፣ በመጊዶንና በየአካባ ቢያቸው ያሉት መንደሮች ነዋሪውን ሕዝብ ስላላስወጡ፣ ከነዓናውያን ኑሮአቸውን በዚያው ለማድረግ ወሰኑ።
28
እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጒልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ፈጽሞ አላስወጧቸውም።
29
እንደዚሁም የኤፍሬም ወገኖች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ማስወጣት አልቻሉም፤ ስለዚህ ከነዓናውያን በመካከላቸው እዚያው መኖርን ቀጠሉ።
30
ዛብሎንም እንደዚሁ በቂድሮንና በነህሎል የነበሩትን በመካከለቸው የቀሩትን ከነዓናውያንን አላስወጣም፤ ነገር ግን የጒልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው።
31
አሴርም በዓኮ፣ በሲዶን፣ በአሕላብ፣ በአክዚብ፣ በሒልባ፣ በኣፌቅና በረአብ የሚኖሩትን አላስወጣም፤
32
በዚህ ምክንያት የአሴር ሕዝብ በምድሪቱ ካሉት ከነዓናውያን ጋር አብረው ኖሩ።
33
ንፍታሌምም በቤት ሳሚስና በቤትዓናት የሚኖሩትን አላስወጣም፤ ስለዚህ የንፍታሌም ነገድ በምድሪቱ ከሚኖሩት ከነዓናውያን ጋር አብረው ኖሩ፤ ይሁን እንጂ በቤት ሳሚስና በቤትዓናት የሚኖሩት ለእነርሱ የጒልበት ሥራ ተገደው ይሠሩ ነበር።
34
የዳን ነገድ በኰረብታማው ምድር ብቻ እንዲወሰን እንጂ ወደ ሜዳማው አገር እንዲወርድ አሞራውያን አልፈቀዱለትም።
35
አሞራውያንም በሔሬስ ተራራ፣ በኤሎንና በሸዓልቢም ኑሯቸውን ቀጠሉ፤ ይሁን እንጂ የዮሴፍ ወገን በበረታ ጊዜ ተገደው የጒልበት ሥራ ከመሥራት አላመለጡም።
36
የአሞራውያን ድንበር አቅራቢያም መተላለፊያ እስከ ሴላዕና ከዚያም የሚያልፍ ነበር።
ኢያሱ 24
መሳፍንት 2
ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21