መሳፍንት

ምዕራፎች 5

መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የዲቦራ መዝሙር

1በዚያን ዕለት ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህን ቅኔ ተቀኙ፤ 2“በእስራኤል ያሉ መሳፍንት ሲመሩ፣ሕዝቡም በፈቃዱ ራሱን ሲያስገዛ፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ። 3“እናንት ነገሥታት ይህን ስሙ፤ገዦችም አድምጡ፤ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ደግሜምለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ። 4“እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ከኤዶም ምድርም በተነሣህ ጊዜ፣ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዝናብ አዘነቡ፤ደመናዎችም ውሃ አፈሰሱ። 5ተራሮች በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት፣በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተናወጡ። 6“በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣በኢያዔል ጊዜ መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ተጓዦችም በጠመዝማዛ መንገድ ሄዱ። 7ለእስራኤል እናት ሆኜእኔ ዲቦራ እስክነሣ ድረስበእስራኤል ያለው የከተማ ኑሮ አበቃለት፤ 8አዳዲስ አማልክትን በተከተሉ ጊዜ፣ጦርነት እስከ ከተማው በር መጣ፤ጋሻም ሆነ ጦር፣በአርባ ሺህ እስራኤላውያን መካከል አልተገኘም። 9ልቤ ከእስራኤል መሳፍንት፣ፈቃደኞችም ከሆኑ ሰዎች ጋር ነው፤እግዚአብሔር ይመስገን። 10“እናንት በነጫጭ አህዮች የምትጋልቡ፣በባለ ግላስ ኮርቻ ላይ የምትቀመጡ፣በመንገድ ላይ የምትጓዙ፣በውሃ ምንጮች ዙሪያ ያለውን፣ 11የዝማሬ ድምፅ ስሙ።ይህም የእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራ፣ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል።“ከዚያም የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ወደ ከተማዪቱ በሮች ወረዱ፤ 12‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤የአቢኒኤል ልጅ ባራቅ ሆይ፤ ተነሣ፤ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ። 13የቀሩትም ሰዎች፣ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ እንደ ኀያል ጦረኛ ወደ እኔ መጣ። 14መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶችከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋር ነበር፤የጦር አዛዥች ከማኪር፣የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ። 15የይሳኮር መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ይሳኮርም ራሱ ወደ ሸለቆው ከኋላውበመከተል፣ ከባርቅ ጋር ነበረ።በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር። 16በበጎች ጒረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ?መንጎችን የሚጠራውን ፉጨት ለመስማት ነውን?በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር። 17ገለዓድ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ዘገየ?አሴር በጠረፍ ቀረ፤በባሕሩ ዳርቻም ተቀመጠ። 18የዛብሎን ሰዎች ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡየንፍታሌም ሰዎች እንደዚሁ በምድሪቱ ኰረብታዎች አደረጉ። 19“ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤የከነዓን ነገሥታት፣ በመጊዶ ውሆች”አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፤ብርም ሆነ ሌላ ምርኮ ተሸክመው አልሄዱም። 20ከሰማያት ከዋክብት ተዋጉ፤በአካሄዳቸውም ሲሣራን ገጠሙት። 21ጥንታዊው ወንዝ፣ የቂሶን ወንዝ፣የቂሶን ወንዝ ጠርጐ ወሰዳቸው፤ነፍሴ ሆይ፤ በኀይል ገሥግሺ 22የፈረሶች ኮቴ ድምፅ በኀይል ተሰማ፤ጋለቡ፤ በኀይልም ፈጥነው ጋለቡ። 23 የእግዚአብሔር መልአክ፣ ‘ሜሮዝን ርገሙ፤’‘ሕዝቧንም አብራችሁ ርገሙ፤ከኀያላን ሰልፍ እግዚአብሔርን ለመርዳት፣በእግዚአብሔርም ጐን ለመቆም አልመጡምና’ አለ። 24‘የቄናዊው የሔቤር ሚስት ኢያዔል፣ከሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን፤በድንኳን ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን። 25ውሃ ለመነ፤ ወተት ሰጠችው፤ለመኳንንት በሚገባ ዕቃ፣ እርጎ አቀረበችለት። 26እጇዋ ካስማ ያዘ፤ቀኝ እጇም የሠራተኛ መዶሻ ጨበጠ፤ሲሣራን መታችው፤ ራሱንም ተረከከችው፤ክፉኛ ወጋችው፤ ጆሮ ግንዱን በሳችው። 27በእግሯ ሥር ተደፋ፤ ወደቀ፤በዚያም ተዘረረ፤ በእግሯ ሥር ተደፋ፤ወደቀ፤ በተደፋበት በዚያ ወደቀ፤ሞተም። 28“የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ?የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች። 29ብልሃተኞች ወይዛዝርቷም መለሱላት፤እርሷ ግን ለራሷ እንዲህ አለች፤ 30‘ምርኮ አግኝተው እየተከፋፈሉ፣እያንዳንዱም ሰው አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረዶች እየወሰደ አይደለምን?ይህ ሁሉ ምርኮ፣ በቀለም ያጌጡ ልብሶችለሲሣራ ደርሰውት፣በጌጣጌጥ የተጠለፉ ልብሶች ለአንገቴይዞልኝ እየመጣ አይደለምን?’ 31“እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፤አንተን የሚወዱህ ግን፣ የንጋት ፀሐይበኀይል እንደሚወጣ እንዲያ ይሁኑ።”ከዚያም በኋላ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።