11 ክፉ ሰው ዐመፅን ብቻ ይፈልጋል፤በእርሱም ላይ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።
12 ተላላን በቂልነቱ ከመገናኘት፣ግልገሎቿን የተነጠቀችን ድብ መጋፈጥ ይሻላል።
13 በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልስ ሰው፣ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም።
14 ጠብ መጫር ግድብን እንደ መሸንቈር ነው፤ስለዚህ ጠብ ከመጫሩ በፊት ከነገር ራቅ።
15 በደለኛውን ንጹሕ ማድረግ ሆነ፣ ንጹሑን በደለኛ ማድረግ፣ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ናቸው።
16 ጥበብን ለማግኘት ፍላጎት ስለሌለው፣ተላላ እጅ የገባ ገንዘብ ጥቅሙ ምንድን ነው?
17 ወዳጅ ምንጊዜም ወዳጅ ነው፤ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል።