5 በድኾች የሚያፌዝ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤በሌላው ሰው መከራ ደስ የሚለው ከቅጣት አያመልጥም።
6 የልጅ ልጆች ለአረጋውያን ዘውድ ናቸው፤ወላጆችም ለልጆቻቸው አለኝታ ናቸው።
7 መልካም አነጋገር ለተላላ አይሰምርለትም፤ለገዥማ ሐሰተኛ አንደበት የቱን ያህል የከፋ ይሆል!
8 እጅ መንሻ ለሰጭው እንደ ድግምት ዕቃ ነው፤በሄደበትም ቦታ ሁሉ ይሳካለታል።
9 በደልን የሚሸፍን ፍቅርን ያዳብራል፤ነገርን የሚደጋግም ግን የልብ ወዳጆችን ይለያያል።
10 መቶ ግርፋት ተላላን ከሚሰማው ይልቅ፣ተግሣጽ ለአስተዋይ ጠልቆ ይሰማል።
11 ክፉ ሰው ዐመፅን ብቻ ይፈልጋል፤በእርሱም ላይ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።