5 በክፉዎች መንገድ ላይ እሾህና ወጥመድ አለ፤ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነዚህ ይርቃል።
6 ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።
7 ባለጠጋ ድኻን ይገዛል፤ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው።
8 ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፤የቊጣውም በትር ይጠፋል።
9 ቸር ሰው ራሱ ይባረካል፤ምግቡን ከድኾች ጋር ይካፈላልና።
10 ፌዘኛን አስወጣው፤ ጠብ ይወገዳል፤ጥልና ስድብም ያከትማል።
11 የልብ ንጽሕናን ለሚወድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።