18 በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር፣እንደ ቈመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ተሳለ ፍላጻ ነው።
19 በመከራ ጊዜ በወስላታ ሰው መተማመን፣በተበላሸ ጥርስና በሰለለ እግር እንደ መታመን ነው።
20 ላዘነ ልብ የሚዘምር፣በብርድ ቀን ልብሱን እንደሚያወልቅ፣ወይም በሶዳ ላይ እንደ ተጨመረ ሆምጣጤ ነው።
21 ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ቢጠማም ውሃ አጠጣው።
22 ይህን በማድረግህም፣ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህ፤ እግዚአብሔርም ዋጋህን ይከፍልሃል።
23 የሰሜን ነፋስ ዝናብ እንደሚያመጣ ሁሉ፣ሐሜተኛ ምላስም ቊጡ ፊት ታስከትላለች።
24 ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር፣በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።