17 ብረት ብረትን እንደሚስል፣ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል።
18 በለስን የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤ጌታውን የሚያገለግልም ክብርን ይጐናጸፋል።
19 ውሃ ፊትን እንደሚያሳይ፣የሰውም ልብ ማንነቱን ገልጦ ያሳያል።
20 ሲኦልና የሙታን ዓለም እንደማይጠግቡ ሁሉ፣የሰውም ዐይን አይረካም።
21 ብር በማቅለጫ፣ ወርቅ በከውር እንደሚፈተን፣ሰውም በሚቀበለው ምስጋና ይፈተናል።
22 ጅልን በሙቀጫ ብትወቅጠው፣እንደ እህልም በዘነዘና ብታደቀው፣ጅልነቱን ልታስወግድለት አትችልም።
23 በጎችህ በምን ሁኔታ እንዳሉ ደህና አድርገህ ዕወቅ፤መንጋህንም ተንከባከብ፤