19 መሬቱን የሚያርስ የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ከንቱ ተስፋን ይዞ የሚጓዝ ግን ድኽነትን ይወርሳል።
20 ታማኝ ሰው እጅግ ይባረካል፤ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ከቅጣት አያመልጥም።
21 አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፤ሰው ግን ለቊራሽ እንጀራ ሲል በደል ይፈጽማል።
22 ስስታም ሀብት ለማከማቸት ይስገበገባል፤ድኽነት እንደሚጠብቀውም አያውቅም።
23 ሸንጋይ አንደበት ካለው ይልቅ፣ሰውን የሚገሥጽ ውሎ ዐድሮ ይወደዳል።
24 ከአባት ከእናቱ ሰርቆ፣“ይህ ጥፋት አይደለም” የሚል የአጥፊ ተባባሪ ነው።
25 ስስታም ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል።