1 የያቄ ልጅ የአጉር ቃል ይህ ነው፤ይህ ሰው ለኢቲኤል፣ለኢቲኤልና ለኡካል ተናገረ፤
2 “እኔ ከሰው ሁሉ ይልቅ ጅል ነኝ፤ሰው ያለው ማስተዋል የለኝም።
3 ጥበብን አልተማርሁም፤ስለ ቅዱሱም ዕውቀት የለኝም።
4 ወደ ሰማይ የወጣ፣ የወረደስ ማነው?ነፋስን በእጁ ሰብስቦ የያዘ ማነው?ውሆችንስ በመጐናጸፊያው የጠቀለለ ማነው?የምድርን ዳርቻዎች ሁሉ የወሰነ ማነው?ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል?የምታውቅ ከሆነ እስቲ ንገረኝ!