6 በእርሱ ቃል ላይ አንዳች አትጨምር፤አለዚያ ይዘልፍሃል፤ ሐሰተኛም ያደርግሃል።
7 “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሁለት ነገር እለምንሃለሁ፤እነዚህንም ከመሞቴ በፊት አትከልክለኝ፤
8 ሐሰትንና ሐሰት መናገርን ከእኔ አርቅልኝ፤ድኽነትንም ሆነ ብልጽግናን አትስጠኝ፤ብቻ የዕለት እንጀራዬን ስጠኝ።
9 ያለዚያ ግን ያለ ልክ እጠግብና እክድሃለሁ፤‘እግዚአብሔር ማን ነው?’ እላለሁ፤ወይም ድኻ እሆንና እሰርቃለሁ፤የአምላኬንም ስም አሰድባለሁ።
10 “አገልጋይን በጌታው ፊት በክፉ አታንሣው፤አለዚያ ይረግምህና ጒዳት ያገኝሃል።
11 “አባቱን የሚረግም፣እናቱን የማይባርክ ትውልድ አለ፤
12 ራሳቸውን ንጹሓን አድርገው የሚቈጥሩ፣ሆኖም ከርኵሰታቸው ያልነጹ አሉ፤