25 ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፣ከኰረብቶችም በፊት ተወለድሁ፤
26 ምድርን ወይም ሜዳዎቿን፣ወይም ምንም ዐይነት የዓለም ትቢያን ከመፍጠሩ በፊት እኔ ተወለድሁ።
27 ሰማያትን በዘረጋ ጊዜ፣በውቅያኖስ ላይ የአድማስ ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፤
28 ደመናትን በላይ ባጸና ጊዜ፣የውቅያኖስን ምንጮች በመሠረተ ጊዜ፣
29 ለባሕር ድንበርን በከለለ ጊዜ፣ውሆችም የእርሱን ትእዛዝ እንዳያልፉ፣የምድርንም መሠረቶች ወሰን ባበጀ ጊዜ፣
30 በዚያን ጊዜ ከጐኑ ዋና ባለ ሙያ ነበርሁ።ሁል ጊዜ በፊቱ ሐሤት እያደረግሁ፣ዕለት ተዕለት በደስታ እሞላ ነበር፤
31 የእርሱ በሆነው መላው ዓለም ሐሤት እያደረግሁ፣በሰው ልጆች ደስ እሰኝ ነበር።