1 መላው የእስራኤላውያን ማኅበር በሴሎ ተሰበሰቡ፣ የመገናኛውንም ድንኳን እዚያው ተከሉ፤ ምድሪቱም ጸጥ ብላ ተገዛችላቸው።
2 ዳሩ ግን ርስት ገና ያልተሰጣቸው ሰባት የእስራኤል ነገዶች ነበሩ።
3 ስለዚህ ኢያሱ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ምድር ለመውረስ ቸል የምትሉት እስከ መቼ ነው?
4 አሁንም ከእያንዳንዱ ነገድ ሦስት ሦስት ሰው ምረጡ፤ እኔም ምድሪቱን ተዘዋውረው እንዲያጠኑና እያንዳንዱም ነገድ መውረስ የሚገባውን ድርሻ ዝርዝር መግለጫ ጽፈው እንዲያመጡ እልካቸዋለሁ፤ ከዚያም ወደ እኔ ይመለሳሉ።